VISIT SOUTH OMO

Contact the business

VISIT SOUTH OMO “Making Ethiopia among the top five tourist destinations in Africa by 2025”. Land of origins

Lake Turkana, formerly Lake Rudolf, lies in the Rift Valley of East Africa.
19/11/2026

Lake Turkana, formerly Lake Rudolf, lies in the Rift Valley of East Africa.

‎ደቡብ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ጸጋዋን ለዓለም ልታሳይ ደግሳለች!‎‎ደቡብ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት፣ ድንቅ ባህሎች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ መዳረሻዎችን እና እምቅ ፀጋዎቿን ለሀገርና ለዓለም ለ...
18/11/2026

‎ደቡብ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ጸጋዋን ለዓለም ልታሳይ ደግሳለች!
‎
‎ደቡብ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት፣ ድንቅ ባህሎች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ መዳረሻዎችን እና እምቅ ፀጋዎቿን ለሀገርና ለዓለም ለማስተዋወቅ "VISIT SOUTH ETHIOPIA EXPO - 2026" የተሰኘ ግዙፍ የቱሪዝም መድረክ በአርባምንጭ ከተማ፣ ጋሞ ባህል ማዕከል ለማካሄድ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
‎
‎ይህ ኤክስፖ በያዝነው ወር ማገባደጃ፣ ከህዳር 26-27/2019 ዓ.ም. የሚከናወን ሲሆን፣ የክልሉን የቱሪዝም አቅም ከሀገራዊና ዓለም አቀፍ ገበያ ጋር የሚያገናኝ፣ አዳዲስ የንግድ ትስስሮችን የሚፈጥር፣ የኢንቨስትመንት በሮችን የሚከፍትና የቱሪዝም ዘርፉን የሚያነቃቃ ታላቅ የጋራ መድረክ ነው።
‎
‎በክልሉ ቱሪዝም ቢሮ እና በግሪን ኤቨንትስ ትብብር የተዘጋጀው ኤክስፖው፣ የባህል ትርዒት፣ የፓናል ውይይት፣ ሚስ ሳውዝ የቁንጅና ውድድር፣ ኤግዚቢሽን፣ የመዳረሻ ጉብኝት፣ ሩጫና ደማቅ የመዝጊያ ኮንሰርትን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።
‎
‎ዝግጅቱን ከ15,000 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኝዎች ይታደሙታል ተብሎ ይጠበቃል።
‎
‎📞 ለተሳትፎ፣ ለአጋርነትና ለተጨማሪ መረጃ፦
‎
‎+251 940 22 21 11
‎+251 913 86 36 02
‎+251 958 19 59 59
‎+251 958 42 59 59
‎+251 958 84 59 59
‎+251 910 33 45 72
‎
‎ደቡብ ኢትዮጵያን ይጎብኙ!
‎ and VisitSouthEthiopia
‎ Region Of Diversity
‎
‎

‎በማህበረሰብ አቀፍ ቱሪዝምና በእንግዳ ተቀባይነት(ukarimu) ዙሪያ ስልጠና በሐዋሣ መሰጠት ተጀመረ‎‎ህዳር 8/2019 ዓ.ም‎‎የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከCBI እና ከኢምፓክት ፎ...
17/11/2026

‎በማህበረሰብ አቀፍ ቱሪዝምና በእንግዳ ተቀባይነት(ukarimu) ዙሪያ ስልጠና በሐዋሣ መሰጠት ተጀመረ
‎
‎ህዳር 8/2019 ዓ.ም
‎
‎የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከCBI እና ከኢምፓክት ፎር ሳስቴነቢሊቲ የማማከር ድርጅት ጋር በመተባበር በማህበረሰብ አቀፍ ቱሪዝምና በእንግዳ ተቀባይነት (UKARIMU) ዙሪያ ያተኮረ የስልጠና መርሐ ግብር በሐዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።
‎
‎ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ ስልጠና፣ የማህበረሰብ አቀፍ ቱሪዝምን ለማጠናከርና የእንግዳ አቀባበል አገልግሎትን ለማሻሻል ያለመ የግንዛቤና የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
‎
‎Ukarimu የሚለው ቃል ከስዋሂሊ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም እንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) ማለት ነው።
‎
‎ስልጠናውን ከኡጋንዳ የመጡት የፕሮግራሙ አስተባባሪ ላቀ ካሱሉ እና አቶ አብርሃም ኤቢሳ እየሰጡ ይገኛሉ።
‎
‎በስልጠናው የአካባቢ አስጎብኚ ማህበራት ሰብሳቢዎች፣ የሆቴል ማኔጀሮች፣ የማህበረሰብ አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻዎች ተወካዮች፣ እንዲሁም የክልልና የዞን የቱሪዝም መዳረሻ አስተባባሪዎች እየተሳተፉ ነው።
‎
‎ አቶ አብርሃም ኤቢሳ እንደገለጹት፣ ስልጠናው በአንድ ዙር ብቻ የሚጠናቀቅ ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
‎
‎ስልጠናው በማህበረሰብ አቀፍ ቱሪዝም ዘርፍ የሚሳተፉ አካላትን አቅም በማጎልበት፣ የእንግዳ አቀባበል ጥራትን በማሳደግና የቱሪዝም ልማትን በዘላቂነት ለማስፋፋት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

17/11/2026

በደቡብ ኦሞ ዞን በኢትዮ ኬንያ ድንበር አቅራብያ የሚገኘው የቱሪካና ሐይቅና የመጨረሻው የቱሪስት የጉብኝት መንደር https://www.facebook.com/share/v/1BthiPWHqG/

‎በደቡብ ኦሞ ዞን  የሚገኙ ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ የቀረፃ ሥራ እየተከናወነ ነው።‎‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በሀገር አቀፍና ዓለም ...
11/11/2026

‎በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ የቀረፃ ሥራ እየተከናወነ ነው።
‎
‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስና የሚዲያ አውታሮች ለማስተዋወቅ የሚያስችል የቀረፃ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
‎
‎የቀረፃ ሥራው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ከኢ.አይ.ኤን ቴክኖሎጂ ድርጅት ጋር በገባው ውል መሠረት እየተከናወነ ሲሆን፣ ዓላማውም የክልሉን ልዩ ልዩ የቱሪዝም ሀብቶች በዘመናዊ የሚዲያ መድረኮች በማስተዋወቅ የክልሉን የቱሪዝም ተደራሽነትና ተወዳዳሪነት ማሳደግ ነው።
‎
‎በዚህ መሠረት በዛሬው ዕለት በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ በሚገኘው ከሆሞሮ ተራራ የቀረፃ ሥራው ተጀምሯል። በተጨማሪም በዳሰነች ወረዳ በመገኘት አስደናቂውን የኦሞ ወንዝ ገጽታ፣ በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የቱርካና ሐይቅ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ መንደሮችን የሚያሳዩ ምስሎች ተቀርፀዋል።
‎
‎የቀረፃ ሥራው በቀጣይ ቀናትም በሌሎች የደቡብ ኦሞ ዞን የቱሪዝም መዳረሻዎች የሚቀጥል ሲሆን፣ ይህም የዞኑን ልዩ የባህል፣ የተፈጥሮና የታሪክ ሀብቶች ለሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ለማስተዋወቅ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።
‎
‎**ደቡብ ኦሞ – የባህልና የተፈጥሮ ድንቅ መዳረሻ!**
‎

11/11/2026

ቱርካና ሀይቅ ዳር - በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኢትዮ ኬንያ ድንበር

Address

Hamer
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when VISIT SOUTH OMO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to VISIT SOUTH OMO:

Shortcuts

Share