15/06/2026
ስፖርት ለጤና፣ አረንጓዴ ልማት ለነገ መተኪያ የሌለው አሻራ! 🌱⚽
በትላንትናው ዕለት በደመቀ ሁኔታ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የኬር ሊቨርስ ማህበራት ስፖርት ፌስቲቫል (Care Leavers Associations Sport Festival) ላይ ከአስደሳቹ የስፖርት ውድድር ጎን ለጎን፣ የ2026 የዓለም የአካባቢ ጥበቃ ቀንን (World Environment Day) በማስመልከት ልዩ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደር በድምቀት ተካሂዷል።
! በሚል መሪ ቃል በተከናወነው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የክብር እንግዶች፣ የወጣቶች ማህበራት አመራሮች፣ የሚዲያ አካላት እና በርካታ ወጣቶች በተግባር በመገኘት የአካባቢ ጥበቃ መልዕክታቸውን አሻራቸውን በማሳረፍ አስተላልፈዋል።
የአረንጓዴ ልማት ንቅናቄ እና ለወጣቶቻችን ያለው ፋይዳ👇
✅️ ሁለንተናዊ ዜጋን ለመገንባት ወጣቱ በስፖርት አካሉንና አእምሮውን እንደሚያጠናክረው ሁሉ፣ ለተፈጥሮና ለሀገር ደህንነትም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ማድረግ የነገ ሀገር ተረካቢነቱን በተሟላ መልኩ ያረጋግጣል።
✅️ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቀነስና ለአካባቢያችን ዘላቂ ጥበቃ ለማድረግ የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና አለው።
✅️ የማህበረሰብ ትስስር እንዲሁም የስራ እድል ፈጠራ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ወጣቶች በአንድነት እንዲሰሩ ከማድረጋቸውም በላይ፣ ወደፊት ከከተማ ግብርና እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ ሰፊ የስራ እድሎችን የመፍጠር አቅም አለው።
👉 የብሔራዊ ኬር ሊቨርስ ማህበራት ጥምረት ኢትዮጵያ National Care Leaver's Associations Coalition Ethiopia (NCLACE) ይህንን የአረንጓዴ ልማት ስራ በስትራቴጂካዊ እቅዱ ውስጥ አካቶ የገዛው ሲሆን፣ ወደፊትም አባል ማህበራትን በማስተባበርና በማንቀሳቀስ ይበልጥ ሰፊና ተከታታይነት ያላቸውን የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ለመምራት ቁርጠኛ ነው።
ወጣቶቻችን በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ያሳዩትን ከፍተኛ ተነሳሽነትና ጉልበት፣ ለሀገራዊ የአረንጓዴ ልማት ጥሪም በተግባር በመመለስ አርአያነታቸውን አሳይተዋል!
የሁላችንም አረንጓዴ አሻራ ለተሻለችና ለለመለመች ነገ! 🌍💚
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
Sports for Health, Green Development for a Sustainable Tomorrow! 🌱⚽
Alongside the thrilling athletic competitions at yesterday's closing of the 1st Care Leavers Associations Sport Festival, a special tree-planting initiative was successfully held at the SOS Children’s Villages compound in Addis Ababa, in commemoration of World Environment Day 2026.
Guided by the inspiring motto, "One Sapling for Tomorrow, One Mark for Nature," youth participants, association leaders, distinguished guests, and media representatives stood together to leave their green legacy and amplify the call for environmental conservation.
The Significance of Green Development for Care Leavers & Youth:👇
♻️ Fostering Holistic Citizenship: Just as sports strengthen the mind and body, engaging in environmental stewardship empowers young people to take active responsibility for their country’s future.
♻️ Combating Climate Change: Active youth climate resilience, reducing ecological degradation, and securing a sustainable environment.
♻️ Community Integration & Green Jobs: Beyond environmental protection, green initiatives foster deep community solidarity and open doors for future economic opportunities through urban agriculture and eco-friendly entrepreneurship.
The National Care Leavers Association Coalition Ethiopia (NCLACE) has institutionalized green development as a core pillar of its strategic plan. Moving forward, the Coalition is fully committed to mobilizing its member associations across the nation to lead larger, structured, and impactful environmental initiatives.
Our youth have powerfully demonstrated that the same energy and passion driving them on the sports field can be channeled to spearhead national green legacy efforts.
Let us all leave our mark for a greener, brighter tomorrow! 🌍💚
SOS Children's Villages in Ethiopia SOS Children's Villages Eastern and Southern Africa Embassy of Denmark in Ethiopia SOS Børnebyerne SOS Children's Villages International የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር / Addis Ababa Youth Association SELAM Fruits Association African Union