31/10/2026
የባህር ዳር ሆቴል ባለሙያዎች እና የበጎ አድራጎት ማህበር የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ!
ከንድፈ ሐሳብ ወደ ተግባር! | ከስልጠና ወደ ብቃት! | ከትብብር ወደ ዘላቂ ውጤት!
በማለት በ17/2/2019 ዓ.ም በክልልና በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ አቶ ጋሸው እንዳላማው፣ የባህር ዳር ከተማ ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ፣ ዶ/ር ኦላፍ፣ የGOPA Worldwide እና GIZ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የማህበራችን አመራሮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ የተጀመረው የአቅም ግንባታ ስልጠና በ21/2/2019 ዓ.ም በስኬት ተጠናቋል።
ስልጠናው ለባህር ዳር ሆቴል ጠቅላላ ሥራ አስኪያጆች (Hotel General Managers)፣ ለሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊዎች (HR Managers) እና ለውስጥ አሰልጣኞች (In-company Trainers) በአጠቃላይ ለ140 የሆቴል ዘርፍ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የሆቴል ኢንዱስትሪውን የአመራር አቅም፣ የሰው ኃይል ብቃት፣ የአገልግሎት ጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ያለመ ነበር።
በስልጠናው የተሸፈኑ ዋና ዋና ርዕሶች
Cooperative Training – የትብብር ስልጠና
Short-Term Training – የአጭር ጊዜ ስልጠና
Green Hospitality – አረንጓዴ የሆቴል አገልግሎት
Digital Hospitality – ዲጂታል ሆስፒታሊቲ
Self-Leadership Mastery – ራስን በብቃት የመምራት ክህሎት
Professionalism and Personal Excellence – ሙያዊነትና የግል ልዕቀት
Brand and Reputation – የሆቴል ብራንድና መልካም ዝና
Brand and Quality Assurance – የብራንድ ግንባታና የጥራት ማረጋገጫ
የስልጠናው ዋና ዓላማ
የሆቴል ኢንዱስትሪው የሚጠይቀውን ዘመኑን የዋጀ አመራር፣ ብቁ የሰው ኃይል፣ ዘላቂ የአገልግሎት ጥራት፣ የዲጂታል አሰራርና ተወዳዳሪ የሆቴል ብራንድ ለመገንባት የሚያስችሉ እውቀትና ክህሎቶችን ማስጨበጥ ነው።
የማህበራችን ምስጋና
ይህንን የአቅም ግንባታ መርሃ ግብር ለማሳካት የገንዘብ፣ የቴክኒክ እና የሙያ ድጋፍ ላደረጉልን GOPA Worldwide Consulting፣ GIZ STEP፣ ለክልልና ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ለባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአሰልጣኞች፣ ለተሳታፊዎችና ለሁሉም አጋሮቻችን በተለይም ለ Dr Olaf ,Mr Alebachew , Mr Alemnew and Bantayehu የባህር ዳር ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ከፍተኛ ምስጋናና አድናቆቱን ያቀርባል።
ይህ ስልጠና የአንድ መርሃ ግብር መጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለባህር ዳር ሆቴል ኢንዱስትሪ የተሻለ አመራር፣ ብቁ የሰው ኃይል፣ የተሻለ የእንግዳ አቀባበል ተሞክሮና ዘላቂ የሙያ ልማት መሠረት የጣለ ትልቅ እርምጃ ነው።
የሆቴል ኢንዱስትሪው ውድድር የሚያሸንፈው በብቁ የሰው ኃይል ነው፤ የብቁ የሰው ኃይል መሠረት ደግሞ ጥራት ያለው ስልጠና ነው!
ባህር ዳር ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር
በትብብር እንገንባ፤ በእውቀት እንዘምን፤ በጥራት እንወዳደር!!!!